አማኑኤል የኢትዮጰያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችው የአምልኮ ፕሮግራም ላይ በአካል ተገኝቶ ለመካፈል እንኳን በደህና መጡ፡፡

የቤተክርስቲያኒቱን ሕንጻ ዳግም ለአገልግሎት ለመክፈት ስንዘጋጅ የቤተክርስቲያኒቱን ማህበረሰብ ጤናና ደህንነት ለማረጋገጥ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ስለዚህ በቤትዎ የሚኖር እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በፕሮግራሙ ላይ በአካል ለመገኘት ባቀዱባቸው ቀናት ስማቸውን አስቀድመው እንዲመዘገቡ እንጠይቃለን፡፡ ይህም በቤተክርስቲያናችን ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ ሰዎችን ቁጥር ለመመጠንና ርቀታቸውንም እንዲጠብቁ በቂ ስፍራ ለማዘጋጀት ይረዳናል፡፡

ከመመዝገብዎ በፊት አስቀድመው ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች፦

 • የኮቪድ በሽታ ምልክቶች ማለትም ትኩሳት፣ ደረቅ ሳል፣ድካም፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ የአይን መቅላት፣ ተቅማጥ፣ራስ ምታት፣ የመቅመስና የማሽተት ስሜት ማጣት፣የቆዳ ላይ ሽፍታ ወይም የእጅና የእግር ጣቶች ቀለም መቀየር፣ የመተንፈስ ችግር ወይም የተቆራረጠ ትንፋሽ፣ የጀርባ ህመም፣ መናገር ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል፣ ወዘተ ከታየቦት እንዲሁም ባለፉት አስራ አራት ቀን ውስጥ በኮቪድ መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ንክኪ ከነበርዎት በቤትዎ በመቆየት በኦንላይን ፕሮግራሙን ይከታተሉ፡፡

 • በቤትዎ ከእርሶ ጋር የሚኖሩ እያንዳንዳቸው የቤተሰብ አባል የራሳቸውን መቀመጫ ወንበር ለማግኘትና በፕሮግራሙ ላይ ለመካፈል እባክዎ በስማቸው ያስመዝግቧቸው፡፡

 • ለልጆችና በአካል የአምልኮ ፕሮግራም መሳተፍ ለማይችሉ ጎልማሶች ፕሮግራሞቻችን በኦንላይን መተላለፉ እንደሚቀጥሉ እንገልጻለን፡፡ ዝርዝር መረሃ ግብራችን በድህረ ገጻችንና በተለያዩ የመረጃ ገጾቻችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

 • በፕሮግራሞቹ ላይ ለመካፈል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድርግ ይጠበቅቦታል፡፡ ነገር ግን አንድ ብቻ ካስፈለጎት ልናቀርብልዎት እንችላለን፡፡

 • የአምልኮ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ ከ20 ደቂቃ በፊት ይገኙ እንዲሁም ተራዎ ደርሶ ወደ ሕንጻው ለመግባት በአስተናጋጆች እስከሚጠሩ ድረስ ከመኪናዎት አይውረዱ፡፡

 • ከእርሶ ጋር በአንድ ቤት ከሚኖሩ የቤተሰብ አባልዎ ውጪ የስድስት(6) ጫማ ርቀት መጠበቅ ይኖርቦታል፡፡ ወንበሮቹ የተዘጋጁት በተገለፀው ርቀት በመሆኑ የአስተናጋጆችን መመሪያ ተከትለው ይቀመጡ፡፡

AEEC Reservation for In-Person Worship

We are pleased to welcome you back for an in-person worship service at Amanuel Ethiopian Evangelical Church (AEEC). As we reopen our church building for in-person services, we will all need to comply with CDC guidelines to ensure our church community’s health and safety.  Therefore, we are asking you to make a reservation for each service you plan to attend.

Things to know before you make a reservation:

 • We kindly ask that you stay at home, if you have any of the symptoms of COVID-19, or if you have been in close contact with a person with a confirmed case of COVID-19 in the last 14 days (Note: Symptoms of COVID-19 include Fever or Chills, Dry Cough, Tiredness, Aches and pains, Sore throat, Diarrhea, Headache, Loss of taste or smell, Difficulty breathing or shortness of breath, Chest pain or pressure, Loss of speech or movement.)
 • Please make a reservation for each person in your family that will need a seat in the worship service.
 • For those who cannot attend in-person services, the ministry to children (Nursery thru Grade 8) will continue to be available online using Zoom. We will post detailed information regarding the children and youth services on the church website and social media sites.
 • Masks are required when you attend service, and will be made available for those who need one.
 • Arrive at least 20 minutes before the service, and wait in your vehicle until the Ushers call you to come into the building.
 • Please keep a physical distance of 6 feet from those who do not live in the same house as you.

Event Info

Date
Location

5411 Franconia Rd. Alexandria, VA 22310

Time

10am