ሻሎም !

ጌታ አጋንንት ደፋልኝ !

 

ቅርብ ጌዜ ይሄ Covid-19 እንዲህ እንቅስቃሴውን ሳይገድበው ብዙ አገልጋይ ወዳቾቼ ከኢትዮጲያ እኔ ወዳለሁባት አገር ብቅ ይሉ ነበር ። እናም ከነዚህ መካከል ካንዱ ጋር ሻይ ቡና እየተባባልን የሆድ የሆዳችንን እየተጫወትን በመሃል አገልግሎትህ እንዴት ነበር ? አልኩት ያው የመድረኩን ማለቴ ነው እንጂ እውነተኛውና ለአእምሮ የሚመቸውማ ሁለንተናን ከሌላው ከልክሎ የጌታ ብቻ ማድረግ እንደሆነ የተገለጠ ነው ፤ ቀበል አድርጎ የሰጠኝ መልስ አስደመመኝ በጣም ጥሩ ነበር ካለኝ በኋላ ጌታም አንድ ሁለት አጋንንት ደፋልኝ ! አለኝ ። አሜን ጌታ አሁንም ለዘላለምም እርኩሳን መናፍስትን ይድፋቸው ብዬ ግን ጌታ አጋንንትን የሚደፋቸው ( ከሰዎች ውስጥ እንዲወጡ )የሚያደርጋቸው ለእኛ ለአገልጋዮቹ ጥቅም ሆነ እንዴ ? አልኩኝ ለካስ እውነቱን ነው ያገልግሎታችን ተቀባይ፣ፈራጅ፣መዛኙና ዋጋን ከፋዩ ጌታ መሆኑ ቀርቶ አገልጋይን ‘አደገኛ!’ሲለንም ‘ዝም ብሎ!’ እያልን ደረጃ መዳቢዎች ከሆንን ከርመናል አገልጋይም አገልግሎቱን መዛኙና በመጨረሻም ዋጋ አስረካቢው ጠሪው መሆኑን ዘንግቶ የዘመኑን ሚዛን ለመድፋት አሳሩን የሚበላው ለዚሁ ነው ግን ይሄ ማለት አገልጋዮች የማይጠየቁ ፣ አይነኬዎች ናቸው ማለቴ አይደለም በዋናነት ተጠሪነታቸው ለጠሪውና በኋላም ለጠያቂው መሆን ግን አለበት እላለሁ ።

    

ለካስ ይሄም ወዳጄ ወዶ አይደለም የጌታን ከሱ ጋር መሆን ‘የአደገኛ’፣ ‘የሃይለኛ’አገልጋይነት ማሳያ ከሆኑት መካከል (በዚህ ዘመን)አንዱ ምልክት ባገልግሎቱ መገለጡ አስደስቶት የነገረኝ ። ቀድሞማ ይሄ እንደ ቃሉ የአማኝ ሁሉ ምልክት ነበር ። አሁንስ ቢሆን ቃሉ መች አረጀና !

 

እንግዲህ በዚህ ጊዜ በውስጤ አንድ ነገር አቃጨለብኝ ። ዋጋዬ ስንት ይሆን ? እነሆ በቶሎ እመጣለው ያለው ጌታ አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና !ብለን ሳንጨርስ ለእያንዳንዱ እንደስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ ። ራእይ 22:12 ብሎ ነቃ ያደርገናል ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ የኖርነው ሕይወትና አገልግሎት ውጤት የሚታየው በጌታ መገለጥ እንደሆነ እያሰብን የአያንዳንዳችን ዋጋም በእጁ ነውና በዚህ ዘመን የተጋነነ ሙገሳ በሚሰጡን (OVER VALUE )በሚያደርጉን ልባችን ሳይግል ደግሞም በሚያንኳስሱን(UNDER VALUE) በሚያደርጉን ልባችን ሳይዝል የዋጋችን ባለቤት የሆነውን የጌታችንና የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በናፍቆት እየጠበቅን ከጌታ መቀበላችንን እርግጠኛ በሆንበት ነገር ሁሉ በትጋት እናገልግል መልዕክቴ ነው ።

 

ሻሎም !

 

በጌታ ወንድማችሁ

ኤልያስ ተ/ሚካኤል

Check out this episode! || ይህንን ክፍል ይመልከቱ!

መንፈሳዊ ውጊያ ክፍል 3

ወደ ኤፌሶን ሰዎች  6:10-20

“10 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። 11 የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። 12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። 13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። 14-15 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ 16 በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። 18 በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤ 19 ደግሞ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ አፌን በመክፈት ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ለምኑ፤ 20 ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልእክተኛ የሆንሁ፥ መናገር እንደሚገባኝ ስለ እርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ለምኑ።”Check out this episode! || ይህንን ክፍል ይመልከቱ!

መንፈሳዊ ውጊያ ክፍል 2

ወደ ኤፌሶን ሰዎች  6 :10

” 10 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። 11 የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። 12 መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። 13 ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። 14-15 እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ 16 በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።”Check out this episode! || ይህንን ክፍል ይመልከቱ!

ማደግህ በነገር ሁሉ ይሁን

by Pastor Aberra

2ኛ የጴጥሮስ መልእክት  1

            “…የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።”

“ሕዝቤ ሆይ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ በርህን ከኅላህ ዝጋ ቁጣው እስኪያልፍ ድረስ ለጥቂት ቀን ተሽሽግ” ኢሳ 26፡ 20

ሕዝቤ ሆይ ሂድ ወደ ቤትህ ግባ
በርህን ከኅላህ ዝጋ ቁጣው እስኪያልፍ ድረስ ለጥቂት ቀን ተሽሽግ
ኢሳ 26፡ 20

ያለ ቀጠሮ በዓለም ላይ ድንገት የተከሰተውን ይህን የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 (በእግዚአብሔር ዓለም ብቻ ቀድሞ የታወቀውን) ሳስብ በአዕምሮዬ የሚመላለሱ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም በዚህ በሰሜን አሜሪካ ካስከተለው በጎ ገጽታ አንዱና ዋናው ስው ሁሉ በግድ በቤቱ እንዲከት መደረጉ ነው ። ባልና ሚስት በገዛ ቤታቸው በፈረቃ በሚኖሩበት ሀገር ብዙዎች በቤታቸው የሚኖሩ ሳይሆን ለቤታቸው በሚኖሩበት ማለትም የቤት ኪራይ ፣ የቤት እዳ ለመክፈል ብዙውን ጊዜያቸውን ከቤታቸው ውጭ ተገደው በሚያሳልፉበት ቤት አለኝ የሚሉና በቤታቸው ግን የማይኖሩ ብዙ በሆኑበት ፤ አብዛኛው ሰው በሩጫ ማሽን ላይ እንዳለ ያለ እረፍት በሚሮጥበት ወላጆች ከልጆች ጋር በቂ ጊዜ ሳይኖራቸው ልጆች የሚያድጉበት ከዚያም ራስ ችለው ለብቻቸው ወደሚኖሩበት ደረጃ በሚደርሱበት የአኗኗር ዘይቤ በምንኖርበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው ። አንድ ወዳጄ ከልጆቼ ጋር በቂ ጊዜ ሳላሳልፍ አደጉብኝ (አደጉልኝ ሳይሆን) እንዳለው ማለት ነው ።

ላልተወሰነ ጊዜም ቢሆን ሁላችን በቤታችን እንድንሰበሰብ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሮብናል:: ስለዚህ እንዲህ አይነቱ ጊዜ ለጌታ ልጆች አስገዳጅ እረፍት (Forced Leave )እንደሚሉት አስገዳጅ የጥሞና ጊዜ ፣ የጸሎት ፣ የጾም ጸሎትና ከቃሉ ጋር ሕብረት የማድረጊያ እርሱ የፍቅር አምላክ ቢሆንም እንደቤተሰብ እርስ በእርስ ያለንን ግንኙነት የማደሻ ጊዜ አድርገን ልንጠቀምበት እንችላለን ።

እንደሚታወቀው በቅጽበት ከውሃና ከመንፈስ ዳግም የተወለደው ማንነታችን የሚያድገው በሂደት ነው ለማደግ ደግሞ ከሚያስፈልጉን ነገሮች ዋናው መንፈሳዊ ስነምግባር ነው:: ገና ወደ ጌታ በመጣንበት (በእርግጥ እሱ ነው ወደኛ የመጣው) በዚያ የተባረከ የክርስትና የመጀመሪያዎቹ አመታት እናደርጋቸው የነበሩ በማለዳ ተነስቶ መጸለይ ቃሉን ማንበብ መጾም መጸለይ ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ማድረግና የመሳሰሉት ነገሮች ሳናውቀው ቀስ በቀስ ከኛ ተወስደውና በሌሎች ነገሮች ተተክተው ያለን የምንመስል የወደቅን ከሆንን ሰነባብተናል ። እናም ይሄ ጊዜ እንደገና የጣልናቸውን እነዚህን እንቁዎቻችንን ለማንሳትና ከጌታ ጋር ያለንን ቃል ኪዳናችንን ለማደስ ወላጆች ለልጆቻችን እነዚህን መንፈሳዊ ስነምግባሮች (Spiritual Discpline ) ለማስተማር እንደ ባልና ሚስትም የተተዉ ወይም ያልነበሩን ለመንፈሳዊ እድገቶቻችን ወሳኝ የሆኑትን ነገሮች ለመጀመርም ይሁን ለማደስ ጥሩ አጋጣሚ ነው እያልኩ ሰውነታችን ያስለመድነውን ነገር ለመልመድና እሱን ለመሆን የተሰራ መሆኑን ልብ ልንል ያስፈልጋል :: እግዚአብሔርን ለመምሰል ራስህን አስለምድ ተብሎ እንደ ተጻፈ ።

በመጨረሻም አንድ ወንድም ያለኝን አንስቼ ልጨርስ ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ በሄደበት ጊዜ በእንግድነት ካሳረፉት ቤተሰብ ጋር የተለያዩ ሰዎችን እያነሳን አገልጋዮችንም ጭምር ስንጫወት ፣ አስተያየት ስንሰጥ ፣ አንዳንዶቹንም ስንተች ቆይተን በመጨረሻም መንፈሴ ቆሽሾ አገኘሁት ። ከዚያ በኅላ ለራሴ ቃል ገባሁ የትም ሃገር ልሂድ ላንድ ሳምንትም ይሁን ላንድ ወር በምቆይበት ቤት ቅዱሳት መጽሓፍትን አብሬያቸው ላጠና ሌላውን ጉዳይ በልክ ላደርግ እንዳለው እኛም ዛሬ ያገኘነውን መልካም አጋጣሚ መቼ ሊያልቅ እንደሚችል አናውቅምና በሁሉም አቅጣጫ ፍሬያማ የምንሆንበት ለማህበራዊ ሚዲያዎች የምንሰጠውን ጊዜ በልክ አርገን የጌታን ፊት የምንፈልግበት የተሃድሶ ጊዜ እንዲሆን ምኞቴም ጸሎቴም ነው ።

ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም

የዮሐንስ ወንጌል  3

1 ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦

2 መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።

3 ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።

Check out this episode!