አማኑኤል የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ 

አማኑኤል የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በስራ ላይ ያለውን የመተዳደሪያ ደንብ  ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ካለችበት እድገት ጋር የተመጣጠነ ሆኖ ባለመገኘቱ የሽማግሌዎች ጉባኤ ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ የሚያዘጋጅ አንድ ኮሚቴ አዋቅሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ኮሚቴውም አሻሽሎ ያቀረበውን  ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ  ለሽማግሌዎች ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የሽማግሌዎች ጉባኤም በተሻሻለው የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ሃሳብ በመስጠትና ሠነዱን በመቀበል በ03/13/2021 በተካሔደው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ለአባላቱ በሪፖርት ማቅረቡ ይታወቃል። 

ጠቅላላ ጉባኤውም በአለም አቀፍ ደረጃ ከተከሰተው በሽታ አንጻር   በተሻሻለው ረቂቅ የመተዳደሪያ ድንብ ላይ ለመነጋገርና ድምጽ ለመስጠት በአካል ለመሰብሰብ አስቸጋሪ መሆኑን በመረዳት  የድምጽ አሰጣጡን ሒደት በኦንላይን እንዲከናወን መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም ተሻሽሎ የቀረበውን የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ለአባላቱ በማቅረብ ድምጽ እንዲሰጥበት የሚያደርግ ኮሚቴ መሰየሙ አይዘነጋም። 

በመሆኑም የቤተክርስቲያኒቱ አባላት የሆናችሁ የተሻሻለውን የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ  በማንበብና በሠነዱ ላይ ድምጽ በመስጠት የአባልነት ድርሻችሁን እንድትወጡ በፍቅር እንጠይቃለን። ነገር ግን በኦንላይን ይህንን ለማድረግ የምትቸገሩ አባላት ካላችሁ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቢሮ በአካል በመገኘትና ረቂቁን በማንበብ በተዘጋጀው የድምጽ መስጫ ሳጥን ውስጥ  የድምጽ መስጫ ካርዳችሁን መክተት የምትችሉ መሆኑን በማክበር እንገልጻለን።

Day(s)

:

Hour(s)

:

Minute(s)

:

Second(s)